የደቡብ ወሎ ዞን የ2008 የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት

(የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራና ድርቅን የመከላከል እንቅስቃሴ)

በዞናችን የተ/ሃብት ልማት ስራ በወረኢሉ ወረዳ ጥር 1/2008 እና ክልላዊ የዓመቱ የተፋሰስ ልማት መክፈቻ በመቅደላ ወረዳ ጥር 3/2008  በማድረግ በይፋ ተጀምሯል  በመሆኑም  1046 ተፋሰሶች በዓመቱ በህዝብ ንቅናቄ ወደ ልማት ገብተዋል   ዞናዊ የሰው ኃይል ጥቅል ተሳትፎ 89% ሲሆን የወንዶች 91% የሴቶች ደግሞ 85% ነው

የወረዳዎች አማካይ የሰው ኃይል ተሳትፎ ሲታይ –ከ90 % በላይ ተሳትፎ ያላቸው 9 (43%) ወረዳዎች (ደሴ ዙሪያ ፤አልብኮ ፣ቃሉ ፣ለገሂዳ፣ከላላ፤ሳይንት ፤ ቦረና ፣ደላንታ እና መቅደላ )

ከ80 እስከ 89% አማካይ ተሳትፎ ያላቸው 10 (48%) ወረዳዎች (አምባሰል ፤ወረባቦ ፤ ኩታበር፤ አርጎባ፤ ወረኢሉ፤ጃማ ፣ወግዲ፤ መ/ሳይንት፤ ለጋምቦ እና ተንታ)

ከ80 % በታች ተሳትፎ ያላቸው 2 (10%) ወረዳዎች (ተሁለደሬና ኮምቦልቻ ከተማ )

ካሉን 501 ቀበሌዎች ውስጥ የህብረተሰብ ተሳትፎ ሲታይ

ከ90% በላይ ተሳትፎ የነበራቸው 300 (60%)

ከ80 እስከ 89% ተሳትፎ የነበራቸው 149  (30%) ቀበሌዎች በአጠቃላይ 449 ቀበሌወች (90 % ) ከ80 በላይ መፈጸም ችለዋል፡፡ ከ80% በታች ተሳትፎ የነበራቸው  52 (10 %) ሲሆኑ ቀበሌን በማቀራረብ  የተሻለ ስራ  ተሰርተል፡፡

ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ/መቅደላ 03

ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ አርጎባ ልዩ ወረዳ እና ወረኢሉ ወረዳ

በተፋሰስ ሞቢላይዜሽን ወቅት መሸፈን የነበረበት 73068 ሲሆን 59078ሄ/ር (81%) መሸፈን ችለናል፡